ሙሐዘ ቅዱሳን (የቅዱሳን ምንጭ) በሚል ርዕስ በዘሪሁን መንግሥቱ የተዘጋጀ ሁለተኛው መጽሐፍ በመንበረ መንግሥት (ግቢ) ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ት/ቤት አዳራሽ ታኅሣሥ 15 ቀን 2010 ዓ.ም. ተመረቀ፡፡
መርሐ ግብሩ በጸሎት ከተጀመረ በኋላ የታኅሣሥ ቅዱስ ገብርኤልን እና የጥምቀት በዓል ለማክበር ከእስራኤል የመጣችው ዘማሪት ማክዳ ቀለመወርቅ የመክፈቻ መዝሙር አቅርባለች፡፡
መርሐ ግብሩ በጸሎት ከተጀመረ በኋላ የታኅሣሥ ቅዱስ ገብርኤልን እና የጥምቀት በዓል ለማክበር ከእስራኤል የመጣችው ዘማሪት ማክዳ ቀለመወርቅ የመክፈቻ መዝሙር አቅርባለች፡፡
የመጽሐፉን ርዕስ ሙሐዘ ቅዱሳን (የቅዱሳን ምንጭ) ብሎ እንደሰየመው አዘጋጁ ሲያብራራ “የፍጥረታት ፈጣሪ፤ የሁሉ ነገር አስገኚ የኾነው እግዚአብሔር በሥራ ለመሰሉት ቅዱሳን “እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ኹኑ” በማለት አስተምሯል /ዘሌ. 19፥21/፡፡ እግዚአብሔር ቅዱስ፣ ፍጹም እንደሆነ ሁሉ እርሱ ያከበራቸው በረድኤት ያደረባቸው፣ በጸጋ የተዋሐዳቸው የሃይማኖት ሰዎች ቅዱሳን ይባላሉ፡፡ ይህንን አምላካዊ ትእዛዝ ሰምተው በተግባር የተረጐሙ፣ ፈጣሪያቸውን ያስደሰቱ፤ ፈጣሪያቸው ያከበራቸውና ያስከበራቸው ሰዎች እንዳሉ ቅዱሳት መጻሕፍት ምስክር ናቸው፡፡ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ በመልእክቱ “ዳሩ ግን እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ኹኑ ተብሎ ስለተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደኾነ፤ እናንተም ደግሞ በኑሮአችሁ ቅዱሳን ኹኑ” በማለት የጸጋ ቅድስና ለቅዱሳን የተሰጠ መኾኑን ያረጋግጥልናል /1ኛ ጴጥ.1፥15/፡፡
ቅዱሳን በሃይማኖት በምግባር እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኙ፣ በንጽሕና በቅድስና ያጌጡ በገድል የተመላ ሕይወት አላቸው፡፡ ለዚህም ነው የነገረ መለኮት ምሁራን /Theologian/ “ያለ ነገረ ቅዱሳን ነገረ እግዚአብሔርን መናገር፣ ያለ ቅዱሳንም እግዚአብሔርን በትክክል ማወቅ አይቻልም” የሚሉት፤ ምክንያቱም ቅዱሳን የእግዚአብሔር መገለጫዎች በመኾናቸው፤ እነርሱን በመመልከት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መናገርና መመስከር ይቻላል፡፡ በአጠቃላይ ነገረ ቅዱሳን የነገረ እግዚአብሔር ትምህርት አንዱ ክፍል ነው፡፡
ቅዱሳን ሀብታቸው ጸጋቸው ከእግዚአብሔር የተገኘ ነው፡፡ ትንቢት ቢናገሩ፣ ድውይ ቢፈውሱ፣ ሙታን ቢያስነሡ ከእግዚአብሔር የተቀበሉትና በስሙ የሚፈጽሙት አገልግሎት ነው፡፡ የቅዱሳን ሥልጣን ምድራዊ ብቻ ሳይኾን ሰማያዊም ነው፡፡ ቅዱሳን በምድር ብቻ ሳይሆን በሰማይም ያለ ማቋረጥ ይለምኑልናል፤ ይጸልዩልናል፣ ያማልዱናል “የጻድቃን ማደሪያቸውን የቅዱሳንን ቦታቸውን አየኹ፡፡ ከዚያም ቦታ ዐይኖቼ ከመላእክት ጋር የሚኖሩበት ማደሪያቸውን ከቅዱሳንም ጋራ የሚኖሩበት ቦታቸውን አዩ፡፡ ስለ ሰውም ልጆች ፈጽመው ይለምናሉ፣ ይጸልያሉ” /ሄኖ.7፣60/፡፡
ሙሐዘ ቅዱሳን የቅዱሳን ምንጭ ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን በፍጹም ሕይወታቸው ለሚመስሉት ቅዱሳን ቅድስናን በተግባር ሠርቶ ሥሩ ያለ፤ ቅዱሳንን የጠራ፣ የተቀበለና ያከበረ እውነተኛው የቅዱሳን ምንጭ /አስገኚ/ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያንም የክርስቶስ አካል በመኾኗ፤ የቅዱሳን ምንጭ ናት፡፡ በመኾኑም ቤተ ክርስቲያንን ከቅዱሳን፤ ቅዱሳንንም ከቤተክርስቲያን መነጠል አይቻልም፡፡ ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ ዘመናት በዓላውያን ነገሥታት፣ በመናፍቃን ብትፈተንም ሙሐዘ ቅዱሳን (የቅዱሳን ምንጭ) ናትና ዐውሎ ነፋሱ፣ ወጀቡ ሳያጠፋት የቆየችው ባፈራቻቸው አያሌ ቅዱሳን ነው፡፡ ቅዱሳን ልጆቿ ወንጌል አስተምረው፣ በገድል ተቀጥቅጠው፣ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቀው ለዚህ ትውልድ እንድትደርስ አድርገዋታል፡፡”
መጽሐፉ በውስጡ ስለያዛቸው ቁም ነገሮች ሲገልጽ “መጽሐፉ በሰባት ምዕራፍ የተዘጋጀ ሲሆን፤ በመጀመሪያው ምዕራፍ የቅድስና ምንነትና ትርጉም፣ ቅድስና የሚሰጠው ለማን ነው? ቅዱሳን የሚባሉት እንማን እንደሆኑ በመግለጽ ስለቅዱሳን ታሪክና ሥራዎቻቸውን ፍንትው አድርጎ ያሳያል፡፡ ሁለተኛው ምዕራፍ ለቅዱሳን የተሰጡ ጸጋዎች ምን ምን እንደኾኑ በስፋት ይዘረዝራል፡፡ በሦስተኛው ምዕራፍ እግዚአብሔር በሕይወተ ሥጋ ላገለገሉትና ላስደሰቱት ለቅዱሳን ባለሟሎቹ በዕለተ ሞታቸው ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡ ይህም ኪዳን ዘላለማዊ በመኾኑ የሚለምኑትን ይቅር ሲላቸውና ሲምራቸው ይኖራል፡፡
ምዕራፍ ዐራት የቅድስና ደረጃዎች (መዓርጋተ ቅዱሳን) ስለሚባሉት ቅዱሳን በተጋድሎ የሚያገኙአቸውን ዐሥሩን ደረጃዎች በዝርዝር ይተነትናል፡፡ ምዕራፍ አምስት የእግዚአብሔር ባለሟል የሆኑ ቅዱሳንን እንዴት ማክበር እንዳለብንና በማክበራችን የምናገኘውን ጥቅም ያስረዳናል፡፡ ምዕራፍ ስድስት የቅዱሳን ተጋድሎ የያዙትን መጻሕፍት ምንነትና የቅዱሳንን ሕይወት ታሪክና ሥራዎቻቸውን በየትኞቹ መጻሕፍት ላይ እንደምናገኝ መረጃ ይሰጠናል፡፡ እነዚህን መጻሕፍት ብናነብ የምናገኛቸውን ጥቅም በስፋት ያትታል፡፡ በመጨረሻም በምዕራፍ ሰባት ከቅዱሳን ተጋድሎ በመማር የራሳችንን የሕይወት ጎዳና እንዴት መምራት እንዳለብን የሚመክሩ ርእሰ ጉዳዮችን የያዘ ነው፡፡” በማለት መጽሐፉን ያዘጋጀበትን ምክንያት አጠቃሏል፡፡
የአዘጋጁን ገለጻ እንዳበቃ የዓምደ ሃይማኖትሰንበት ት/ቤት መዘምራን ያሬደዊ መዝሙር አቅርበዋል፡፡
መጽሐፉ ሲዘጋጅ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የአርትኦት ሥራውን የተወጡት ቀሲስ ሰሎሞን ወንድሙ መጽሐፉ ስላለው ጠቀሜታ የሚከተለውን አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
“ቅድስና የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ በመኾኑ ዘወትር ቅዱስ እምቅዱሳን፣ ልዑል እምልዑላን፣ አምላከ አማልክት፣ እግዚአ አጋእዝት ወንጉሠ ነገሥት በማለት እንጠራዋለን፡፡ የልዑል እግዚአብሔር ቅድስና በባሕርዩ የነበረና የሚኖር፣ ከፍጡራን የተለየ፣ ተነጻጻሪ የሌለውና በቃላት ይኽንን ይመስላል የማይሉት ፍጹም ነው፡፡
በኦሪት ዘሌዋውያን ምዕራፍ ፲፩ ቁጥር ፵፭ ላይ እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ኹኑ፡፡ በማለት እንደተናገረው አስቀድሞ ከእናታቸው ማኅጸን የመረጣቸውን፣ ለአገልግሎት የጠራቸውን፣ ያጸደቃቸውንና ያከበራቸውን ቅዱሳን በማለት እንጠራቸዋለን፡፡
Continue reading →