በጎ ሰዎችን ለማፍራት በጎ የሠሩትን እንሸልም

በጎ ሰዎችን ለማፍራት በጎ የሠሩትን እንሸልም

Gegna 3D Model

ሦስተኛው ዙር የበጎ ሰው ሽልማት በዐሥር የመወዳዳሪና ዘርፍ በአክሱም ሆቴል ነሐሴ 30 ቀን 2007 ዓ.ም ተካሔደ፡፡ የ “እንኳን ደህና መጣችሁና አደረሳችሁ” መልእክት በሙሐ ዘጥበባት ዳንኤል ክብረት የበጎ ሰው ሽልማት የቦርድ ሰብሳቢ ተላላፏል፡፡ ተቋሙ በባለፉት ሦስት ዓመታት የሠራቸው ሥራዎችና ያጋጠሙት ችግሮች ምን እንደነበሩና በሀገራችን ከዚህ ቀደም ሽልማት ይሰጡ የነበሩ ተቋማት ለምን መቀጠል እንዳልቻሉ ጥናት ተደርጎና ትምህርት ተወዶ ሥራው እንደተጀመረ ካስተላለፉት መልእክት ለመረዳት ተችሏል፡፡

ከሙሐ ዘጥበባት ዳንኤል የመክፈቻ ንግግር በኋላ አምባሳደር ዘውዴ ረታ በጎነት ምንድን ነው? ለሀገር መሥራትስ? ለሚለውን ጥያቄ መልስ ሊሰጥ የሚችል ንግግር “በጎነት ደካማው ስንፍናውን ትቶ ወደ ተሻለ አስተሳሰብ የሚያደርስ የቅኖች መንገድ ነው፡፡ የሰው ልጅ በዚህ ዓለም ሲኖር ለሀገሩ ነጻነት ለወገኑ አንድነት ዘር፣ ቀለም፣ ሃይማኖት ሳይገድበው መሥራት ይኖርበታል፡፡ የሀገር ነጻነትና አንድነት ከሌለ በዚህ ዓለም ምንም ነገር ሊኖር አይችልም፡፡ በጎ ሰዎች ይህን አስተሳሰብ በተከታዮቻቸው ላይ ማሳደር የሚችሉ ናቸው” በማለት ይመክሯቸው የነበሩትን የመኮንን ሀብተ ወልድ የቀድሞ የሀገር ፍቅር ቲአትር ቤት ሥራስኪያጅ አባባል በመጥቀስ ታዳሚውን ያስደሰተ ንግግር አድርገዋል፡፡

39ከሳቸው አስተማሪ ንግግር በኋላ የበጎ ሰው ሽልማት አስተባባሪ የበጎ ሰው ሽልማት ከባለፉት ሁለት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር በመወዳደሪያ ዘርፍና በተሸለሚ እጩዎች ብዛት ጨምሮ እንደመጣ ከአዘጋጅ ኮሚቴው አስተባባሪ ሪፖርት ለመገንዘብ ችለናል፡፡

Capital Hotel

በዐሥር የመወዳዳሪያ ዘርፎች እጬዎች እንዲጠቆሙ የበጎ ሰው ሽልማት አዘጋጅ ኮሚቴ መስፈርቱን ለጠቋሚዎች ያስተዋወቀው በታኅሣሥ ወር 2006 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ነበር፡፡ በተሰጠው በጎ ሰዎችን የመጠቆም እድል በገጸ ድር፣ በኢሜልና በፖስታ ቁጥራቸው 250 የሚጠጉ እጩ ተሸላሚዎች ለአዘጋጅ ኮሚቴው ከአዲስ አበባ፣ ከክልል ለተሞችና ከውጪ ሀገራት ተጠቁመዋል፡፡ የአዘጋጅ ኮሚቴ አድካሚ ሥራ የሚጀምረው በጥቆማ የደረሱትን እጩዎች ማንነት በማጥናት የሠሯቸውን ሥራዎች ለዳኞች ማቅረብ ነው፡፡

የእነዚህ በጎ ሥራ የሠሩ እጩዎችን ማንነት በማጣራት አዘጋጅ ኮሚቴው በዐሥር ዘርፍ የተጠቆሙ ግለሰቦች ዳኝነት ለመስጠት እንዲያመች በእያንዳንዱ ዘርፍ አምስት ሰዎችን መርጦ ለዳኞች አርባ አምስት እጩዎችን ብይን እንዲሰባቸው አድርጓል፡፡ ዳኞቹም የቀረቡትን ተሸላሚ እጩዎች ማንነት የያዘ ግለ ታሪካቸውን በመመርመር በእያንዳንዱ ዘርፍ ተሸላሚ የሆኑት አባላት እንደሚከተለው ይፋ አድርገዋል፡፡

46

የበጎ ሰው እጩ የ2007 ዓ.ም. ተሸላሚዎች

1 በሳይንስ ዘርፍ ፕሮፌሰር አበበ በጅጋ                     

2 በሥነ ጥበብ ዘርፍ ሰዓሊ ታደሰ መስፍን
3 በጎ አድራጎት ዘርፍ ትርሐስ መዝገበ                       

4 በማኅበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ደሳለኝ ራሕማቶ
5 በስፖርት ዘርፍ ዶ/ር ወ/መስቀል ኮስትሬ             

6 በመንግሥታዊ ሓላፊነትን በመወጣት ሽመልስ አዱኛ
7 ሚዲያና ጋዜጠኝነት ያዕቆብ ወ/ማርያም               

8 በንግድ ሥራ ፈጠራ ዘርፍ ሰላም ባልትና 

9 ቅርስና ባሕል ዘርፍ ሀብተ ሥላሴ ታፈሰ              

10 ልዩ ተሸላሚ ፊታውራሪ አመዴ ለማ

በሰላም ዘርፍ የተጠቆመ እጩ እጩ ተወዳዳሪ ባለመኖሩ በዚህ ዓመት መሸለም እንዳልተቻለ የዚህ ዝግጅት ጸሐፊ ከነበሩት ከአቶ ቀለመወርቅ ሚደቅሳ ገለጻ ተገንዝበናል፡፡

32

የዕለቱ ልዩ ተሸላሚ በመሆን በአስተባባሪ ኮሚቴው የተሸለሙት ፊታውራሪ አመዴ ለማ ነበሩ፤ “በጎነት ሃይማኖት፣ ዘር፣ ብሔርና ቀለም እንደማይስነው በሕይወት እያሉ ከሠሩአቸው በጎ ተግባራት ለመማር ችለናል” ሲል መርሐ ግብሩ እየተካሔደ በእንባ ጭምር አስተያየቱን ከሰጣት አንድ ታዳሜ ለመረዳት እንደቻለች በስፍራው ተገኝታ ዘገባውን ካደረሰችን ጦማሪያችን ለመረዳት ችለናል፡፡
በእያንዳንዱ ዘርፍ አሸናፊ የሆኑ ተወዳዳሪዎች ግለ ታሪካቸው ተጋባዥ በሆኑ ጋዜጠኞች፣ አርቲስቶችና ምሁራን ለታዳሚው እንዲነበብ ተደርጎል፡፡ የበጎ ሰው ተሸላሚዎች ከሠሩት ሥራ ሌሎች እንዲማሩበት ምክንያት ሆኗል፡፡ ግለታሪካቸውን የያዘም መጽሔት ለታዳሚው በነጻ ታድሏል፡፡
በአክሱም ሆቴል ተገኝታ የ2007 ዓ.ም የበጎ ሰው ሽልማት መርሐ ግብር ተከታትላ መረጃውን ያደረሰችን ጦማሪት “በጎ ሰዎችን በብዛት ለማፍራት በጎ ለሠሩ ሰዎች እውቅና እንስጥ! እንሸልማቸውም” በሚል መልክእክቷ ተሰናበተችን፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ” ብሎ እንዳስተማረን እድሜ ቢሰጠን በሚቀጥለው ዓመት አራተኛው ዙር ሽልማት የበጎ ሰው ሽልማት በኅዳር ወር 2008 ዓ.ም. ሥራውን ይጀምራል፡፡ በጎ የሠራን ሰው በመጠቆም ሥራውን በማስተዋወቅ፣ እውቅና መስጠትና ለመሸለም ተቋሙ የሚሠራውን ሥራ በመደገፍ ተባባሪ እንሁን! /ሮሜ 12፥9/፡፡

አስተያየት ያስቀምጡ